እብናትወረዳ በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የሚገኝ ሲሆን በምዕራብ ከሊቦከምከም ፣በደቡብ ከፋርጣ ወረዳ ፣ በሰሜን ከምስራቅ በለሳ ወረዳ፣በሰ/ምዕራብ ከምዕራብ በለሳ ወረዳ፣በምስራቅ ከዋግህምራ ዞንደሀና እና ቡግናወረዳዎች፤ በደቡብምስራቅ ከመቀጣዋ ወረዳ ጋር ይዋሰናል፡፡
ወረዳው አጠቃላይ209, 243በላይ ህዝብ የሚኖርበት ሲሆን በሶሰት የኑሮ መሠረት ዞኖች (Livelihood Zones)ውስጥ ማለትም በተከዜ ቆላማ ማሽላና ፍየል(TSG)፣ሰሜን ምስራቅ ወይና ደጋ ድብልቅ እህል (NMC) እና ጣና ዙሪያ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን 1731 ኪ.ሜ2 (173,100) ሄ/ርይሸፍናል (ምስል 5ን ተመልከት)፡፡
አብዛኛው የወረዳው ህዝብ የሚተዳደረው በግብርና ስራ ሲሆን፤እብናት ወረዳ በአማራ ክልል ከሚገኙ በአየር ንብረት ተለዋዋጭነት በከፍተኛ ሁኔታ ከሚጎዱ (የድርቅ አደጋ ስጋት) ካለባችው ወረዳዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ በወረዳው 29 የገጠር ቀበሌዎች እና 2 የከተማ ቀበሌዎች ያሉት ሲሆን በውስጡ ደጋ (6 ቀበሌዎች)፣ወ/ደጋ 8 ቀበሌዎች እና ቆላ 15 ቀበሌዎች አግሮ-ኢኮሎጅ ይይዛል፡፡