የ10 ቀን ምክረ ሃሳብ
ለ ጣና ላይቭሊሁድ
Advisory for Weather Forecast
በመጠንም ሆነ በሥርጭት ቀስ በቀስ ከሰሜን ምሥራቅ ላይ እየቀነሰ ወደ ምዕራብ አጋማሽ የክልሉ ክፍሎች ላይ እየተስፋፋ ይሄዳል፡፡ በተጨማሪም ምዕራብና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምሥራቅ ጎጃም እንዲሁም አዊ ዞን፣ በአብዛኛው ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ የሚኖራቸዉ በመጪው ሜይ ሁለተኛው አሥር ቀናት ለዝናብ መኖር አመቺ ሁኔታ የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በተለይም ዋና የዝናብ ወቅት አካባቢዎች ሜይ የተሻለ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማለ፡፡ በአጠቃላይ በቀጣይ አስር ቀናት፣ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ዋግኸምራ፣ ከፊል ምስራቅ ጎጃም፣ ጥቂት የደቡብ ጎንደር ዞኖች ፣ ኦሮሚያ ልዩ ዞን እና የሰሜን ሸዋ ዞኖች በአብዛኛው ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡የተቀሩት የክልለ አካባቢዎች በአመዛኙ ዳመናማ ሆነው ይሰነብታለ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖር የደመና ሽፋን አንፃር፣በአንዳንድ ቆላማ ስፍራዎች ወበቃማ የአየር ሁኔታ እንደሚኖር ይጠበቃል፡፡
የአግሮ ሜትርኦሎጂ የሰብል ክትትል ሁኔታን መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ ምክረ-ሃሳብ
ከሊይ በተሰጠው የአየር ሁኔታ ትንበያ መሰረት በሚቀጥሇው የሜይ የመጀመሪያው አስር
ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮልጂ ገጽታዎች በተሇያዩ የክልሊችን ሥፍራዎች በተሇይም
በምዕራብ ጎጃም፣ በደቡብ ጎንደር፣ በአዊ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በደቡብና ሰሜን ወሎ ዞኖች ሊይ
መደበኛና ከመደበኛው በሊይ መጠን ያሇው ዝናብ እንዲሁም በምስራቅ ጎጃም ከመደበኛዉ ጋር
የተቀራረበ ዝናብ ሉኖራቸዉ እንደሚችል የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማለ፡፡ ይህም ሁኔታ
የበልግ አብቃይ በሆኑት አካባቢዎች ሇሚያከናውኑት የግብርና ስራ እንቅስቃሴ አመቺ ሁኔታን
እንደሚፈጥር የሚጠበቅ ሲሆን፤ በተሇይም የሚገኘዉ እርጥበት በተሇያየ የዕድገት ደረጃ ሊይ
ሇሚገኙ ልዩ ልዩ ሰብልች፣ ሇቋሚ ተክልች የዉሃ ፍሊጎት መሟሊት ሇግጦሽ ሳርና ሇመጠጥ
ዉሃ አቅርቦት መሻሻል የጎሊ አስተዋፅኦ እንደሚኖረዉ ይጠበቃል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚገኘዉ
እርጥበት ሇእርሻ ስራ እንቅሥቃሴ አመቺ ሁኔታን የሚፈጥር ቢሆንም የአፈር መታጠብን
በአንዳንድ አካባቢዎች ሉያስከትል ስሇሚችል ተጋሊጭ የሆኑ አካባቢዎች ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ
ማድረግ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም እርጥበት አጠር በሆኑ አካባቢዎች የሚገኘውን ውኃ
የተሇያዩ የዉሃ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን በመጠቀም በመካከል ሉኖር በሚችል ደረቅ ሰሞናት
መጠቀም አስፈሊጊ ነዉ፡፡
የውሃና መስኖ ሁኔታን መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ ምክረ-ሃሳብ
እ.ኤ.አ ከሜይ 01-10/2022 የአየር ሁኔታ በውሃው ዘርፍ እንቅስቃሴ ሊይ ሉያሳድር
የሚችሇዉ ተፅዕኖ
ከሊይ በተሰጠዉ ትንበያ መሰረት በሚቀጥለት የሜይ ወር የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት
በአብዛኛዎቹ የክልሊችን ዋና ዋና ተፋሰሶችና ወንዞች ሊይ የተሻሇ እርጥበት እንደሚኖራቸው
ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም በአብዛኛው ግልገል አባይ፣ የሊይኛዉና መካከሇኛዉ አባይ፣ የታችኛው
ተከዜ፣ ርብና በሇስ ተፋሰሶች ሊይ ከመጠነኛ እርጥበት እስከ እርጥበታማ የደረሰ እርጥበት
እንደሚያገኙ ይጠበቃል፡፡ ይህም ሁኔታ ሇገፀ ምድርና ሇከርሰ ምድር ውሃ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡