ወቅታዊ ምክረ ሃሳብ
ለ ጣና ላይቭሊሁድ
Advisory for Weather Forecast
የክረምት 2021 ወቅት የሚቲዎሮሎጂ ትንበያን መሠረት በማድረግ በተለያዩ ዘርፎች የተሰጠ ምክረ ሃሳብ
- የሚቲሮሎጅትንበያንመሰረትበማድረግለአርሶ አደሩየኤክስቴንሽንአገልግሎትመስጠት፤
- ለአመራሩ፤ ለባለሙያውና ለአ/አደሩ በወቅቱ የመኸር ዝናብ ሁኔታ እውቅና መስጠት፤
- ከዚህ በፌት በተደራጀው ኤክስቴንሽንአደረጃጀቶችመሰረትበማድረግ ለአ/አደሩ የክረምት ወቅታዊ የግብርና ስራ እንቅስቃሴወችን እንዲሰሩ ማድረግ (የማሳ ዝግጅት፣ የዘር መረጣ፣ የግብዓት አጠቃቀም እንዲሁም አዳዲስ የግብርና ቴክኒወሎጅወችን እንዲጠቀሙ መምከር)
- ለክረምቱ ለሚከናወነው የሰብል ልማት እንቅስቃሴወችን የእርሻ ድግግምሽን በሰፊው ማካሄድ፤
- እንደየላይብሊሁድ ዞኑ ተስማሚ የሆኑ የሰብል ዘሮችን የመለየት ስራ መስራት (ምርጥ ዘር፣በምርጥ ዘር ያልቀረቡትን ስብሎች የተሸሉ የስብል ዘሮችን ልውውጥ በማድረግ ና የማበጠር ስራ ማከናወን፤
- ሰብሎች በመሰመር እዲዘሩ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ እንዲከናወን ትምህርት መሰጠት፤
- የኮምዲቲ ሰብሎችን በክላስተር እንዲዘሩ ማድረግ( ጤፍ ፣ስንዴ፣ማሾ… )፤
- የዘር ወቅቶችን ጠብቆ በየላይብሊሁድ ዞኑ ሁሉንም የሰብል አይነቶች እንዲዘሩ የምክረ አገልግሎት መስጠት፤
- በአጠቃላይ ከላይ ያልተዘረዘሩትን ሰብሎችንም ከዚህ በፌት ሲዘሩበት ከነበረው የመዝርያ ቀናቶች ቀድመው እንዲዘሩ ምክረ ሃሳብ መሰጠት፤
- የግብርና ግብዓቶችን አጠቃቀማችን በወቅቱና በስፍት እንዲሁም በየላይብሊሁድ ዞኑ በምክረ ሃሳቡ መሰረት እንዲጠቀሙ ትምህርት መሰጠት፡፡ (ማዳበርያ፦ ዬርያ፣ኤንፒኤስ፣ህያው ማዳበርያ)፣ (ምርጥ ዘር ሰንዴ፣ጤፍ፣ በቆሎ ፣ ሩዝ….) እንዲሁም ታይሬጅር ና ቢቢኤም፤
የአግሮ ሜትርኦሎጂ የሰብል ክትትል ሁኔታን መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ ምክረ-ሃሳብ
የክረምት 2021 ወቅት የሚቲዎሮሎጂ ትንበያን መሠረት በማድረግ በተለያዩ ዘርፎች የተሰጠ ምክረ ሃሳብ
ግብርና (ኤክስቴንሽን ፣ሰብል ልማት ፣አዳጋ መከላከልና እንሰሳት ሃብት ልማት)
- የሚቲሮሎጅትንበያንመሰረትበማድረግለአርሶ አደሩየኤክስቴንሽንአገልግሎትመስጠት፤
- ለአመራሩ፤ ለባለሙያውና ለአ/አደሩ በወቅቱ የመኸር ዝናብ ሁኔታ እውቅና መስጠት፤
- ከዚህ በፌት በተደራጀው ኤክስቴንሽንአደረጃጀቶችመሰረትበማድረግ ለአ/አደሩ የክረምት ወቅታዊ የግብርና ስራ እንቅስቃሴወችን እንዲሰሩ ማድረግ (የማሳ ዝግጅት፣ የዘር መረጣ፣ የግብዓት አጠቃቀም እንዲሁም አዳዲስ የግብርና ቴክኒወሎጅወችን እንዲጠቀሙ መምከር)
- ለክረምቱ ለሚከናወነው የሰብል ልማት እንቅስቃሴወችን የእርሻ ድግግምሽን በሰፊው ማካሄድ፤
- እንደየላይብሊሁድ ዞኑ ተስማሚ የሆኑ የሰብል ዘሮችን የመለየት ስራ መስራት (ምርጥ ዘር፣በምርጥ ዘር ያልቀረቡትን ስብሎች የተሸሉ የስብል ዘሮችን ልውውጥ በማድረግ ና የማበጠር ስራ ማከናወን፤
- ሰብሎች በመሰመር እዲዘሩ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ እንዲከናወን ትምህርት መሰጠት፤
- የኮምዲቲ ሰብሎችን በክላስተር እንዲዘሩ ማድረግ( ጤፍ ፣ስንዴ፣ማሾ… )፤
- የዘር ወቅቶችን ጠብቆ በየላይብሊሁድ ዞኑ ሁሉንም የሰብል አይነቶች እንዲዘሩ የምክረ አገልግሎት መስጠት፤
- በአጠቃላይ ከላይ ያልተዘረዘሩትን ሰብሎችንም ከዚህ በፌት ሲዘሩበት ከነበረው የመዝርያ ቀናቶች ቀድመው እንዲዘሩ ምክረ ሃሳብ መሰጠት፤
- የግብርና ግብዓቶችን አጠቃቀማችን በወቅቱና በስፍት እንዲሁም በየላይብሊሁድ ዞኑ በምክረ ሃሳቡ መሰረት እንዲጠቀሙ ትምህርት መሰጠት፡፡ (ማዳበርያ፦ ዬርያ፣ኤንፒኤስ፣ህያው ማዳበርያ)፣ (ምርጥ ዘር ሰንዴ፣ጤፍ፣ በቆሎ ፣ ሩዝ….) እንዲሁም ታይሬጅር ና ቢቢኤም፤
ከእንሰሳት አንፃር
- ያለውን ምቹ ሆኔታ በመጠቀም ለወቅቱ ተስማሚ የሆኑና የተሸሻሉ እንሰሳት መኖወችን እንደ መኖ ጓ ያ፣ የርግብ ዓተር ፣ ላብ ላብ ፣የላም አተር የመሳሰሉትን በሁሉም ላብሊሁድ ዞን እንዲያለሙ ትምህርት መሰጠት ፡፡
- በተከለሉ ተፍሰሶችና የግጦሽ መሬቶች ላይ የሚደረሱ መኖወችን እጭደው እንዲመግቡ ትምህርት መሰጠት ፡፡
- የሚኖረውን የዝናብ ሰርጭት ለእንሰሳት እርባታ ምቹ ሆኔታ ሰለሚፈጥር ምርታማና የተሻሻሉ ዝርያወችን እንዲያረቡ ትምህርት መሰጠት ፡፡
- በመደበኛ ሁኔታ ለሚከሰተ በሽታወች የቅደመ ክትባትና እርጭት ሰራወችን እንዲሰሩ ትምህርት መሰጠት ( በተለይ በተከዜ ላይብሊሁድ ዞን ላይ አንትራክስና አባሰንጋ በሽታወች ላይ )፤
- የእንሰሳት ተዋፅዓ ምርቶችን እንደ ወተት፣ቅቤ ፣ ስጋና የቆዳና ሌጦ ምርቶችን ወደ ገብያ እንዲያቀርቡ ትምህርት መሰጠት፤
- የእንሳስት መጠለያን የማደስና የክረምት ዝናብ እንዲቋቋም አደርጉ መስራት እንዳለባቸው ትምህርት መስጠት፤
- ከንብ ማነብ አንፃር ኬሚካል ሲጠቀሙ ንቦች በማይወጡበት ስዓት እንዲረጮ ትምህርት መስጠት(ከቀኑ11፡00 በኋላ መርጭት)፤
- ክረምቱ የተስተካከለ የቀሰም ወቅት በመሆኑ ንቦችን ከባህላዊ ቀፎ ወደ ተሻሻለ ቀፎ እንዲገለብጡ ትምህርት መስጠት፤
- የዝናብ ሆኔታን በየቀኑ በመከታተል እለታዊና ሳምንታዊ መሪጃ መለዋወጥ፤
- በጉርፍ ተጠቂ ለሆኑ ቀበሌዎች (ደረግሃ፣እንባጭኮ፣ሹምጌ፣ ሰለማያ፣አበገልዲ፣ ወንበሮች፣ጉናጉና፣ሰራውዲ …) የክረምቱን ዝናብ ተከትሎ የጉርፍ አዳጋ ሰለሚኖር ማ/ሰቡ እራሱን ከአድጋ እንዲጠብቅ ትምህርት መስጠት፤ በክርምቱ ወቅት የሚደረሱ አዳጋወችን በቀበሌው የአዳጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሜቴ እያረጋገጡ በፎርሙመሰረት የተጠቃለለ ሪፖርት ወደ ወረዳ መላክ፤
የውሃና መስኖ ሁኔታን መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ ምክረ-ሃሳብ
ከመጠጥ ውሃው አንጻር፡-
- የመጠጥ ውሃ መጠናቸው ስለሚጨምር በቀን መጠቀም ያለባቸውን የውሃ ፍጆታ መጠቀም እዳለባቸው፤
- የመጠጥ ውሃዎች ሊበከሉ ስለሚችሉ ወቅቱን የጠበቀ የውሃ ምርመራ እና ማከሚያ ኬሚካል (ክሎሪን፤ውሃ አጋር፤ፒዩሪፈር እና አኳታብስ) እዲጠቀሙማድረግ፤
- አ/አደሩ እደ አረም ማጥፊያ እና ማዳበሪያ ያሉ ኬሚካሎችን ሲጠቀም ቢያንስ 10ሜትር ዙሬውን መተው እና የንፁህ መጠጥ ውሃን በማይበክል መንገድ መጠቀም እዳለበት ግንዛቤ መፍጠር፤
- የውሃ ማቆሪያ ኩሬዎችን በቂ ውሃ እዲይዙ እና ለቀጣይ ለንጹህ መጠጥ አገልግሎት እዲሰጡ የቅድመ ዝግጅት ስራ መስራት አለባቸው (ባላርብ፤ብርኮች፤ አቋሽሞች፤ጥጋጌ እና ቅጣ)፤
- የንጹህ መጠጥ ውሃ ተቋማት በክረምት ዝናብ ምክንያት ሊበከሉ ስለሚችሉ በአጥር ዙሬውን እዲታጠር እና የጎርፍ መቀልበሻ እዲያዘጋጁ ማድረግ አለባቸው፤
- የሚዘንበው ዝናብ የተስተካከለ ሊሆን ስለሚችል ለቀጣይ ለልዩልዩ አገልግሎት እዲውል እሮቶዎችን በማዘጋጀት የጣራላይ ውሃ እዲያሰባስቡ ማድረግ በተለይ በቀጣይ የበጋ ወራት የውኃ እጥረት በሚገጥምበት አካባቢ (ባላርብ፤ብርኮች፤ አቋሽሞች፤ጥጋጌ እና ቅጣ)፤
Advisory for Health & Nutirition
ከጤና አንጻር
በጣና ተፋሰስ (ዝሃ፣ ሰራውዲ፣ ጣራሲንባ፣ ዋጌ እና ወርጋጃ) በክረምቱ መውጫና መግቢያ ለወባ በሽታ ተጋላጭ ሊሆኑ ስለሚችሉ፦
- ወባ ትንኝ ሊራቡበት የሚችሉትን ቦታዎች በመለየት የማዳፈን ፤የማጨድና ያቆሩ ወሃወችን ያማፋሰስ እና የመረበሽ ስራወች ተከታታይት ባለው መልኩ ቢሰሩ
- በወባ መያዙ የተረጋገጠ ከሆነ የታዘዘለትን/ላትን መድሃኒት የጤና ባለሙያው ባዘዘው መሰረት መውሰድ
- ሙቀት ያለበት ሁሉ በቅርብ ወዳለ ጤና ተቋም ተሎ መሄድና መመርመር
- የአልጋ አጎር በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል በተለይ ማታ ማታ ላይ
- የአልጋ አጎበርን ለሌላ አገልግሎት መጠቀም ባይችሉ
- በርጭት ወቅት ቤትን ተከታትሎ ማስረጨት